47ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብስባ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።
ስብሰባው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።
በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማትና የሕብረቱ አመራሮች፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።
ስብስባው የካቲት 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ እንዲሁም የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚከናወነው 37ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የአፈጻጸም እንዲሁም ሕብረቱ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2023 ያካሄዳቸውን ስብስባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል።
የሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል።




All reactions:
33
ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ከሶማሌ ላንድ መንግስት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች ።
ይህን ምክንያት በማድረግ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣መንግሥት ሰራተኞች፣ ተማሪዎች በተገኙበት በአሶሳ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ አደረገ። በተደረገው የመግባቢያ ሠነድ ማህብረተሰቡ በተለያዩ ፕሮግራሞች ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ።
