በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአለም አቀፍ ለ26ኛው ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ14ኛው ጊዜ “ብዝህሃነትን መኖር” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የአብሮነት ቀንን አሰመልክቶ በአሶሳ ከተማ በድማቅ ሁኔታ ተከብሯል!

“ብዝሀነትን መኖር በሚል መሪ ሀሳብ ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን በመከበር ላይ ይገኛል።

በበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ ፅ/ቤትም “አብሮነትን ለማጠናከር የሚተጋ አመራር” በሚል መሪ ቃል መርሀ ግብሩ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረው በአል በያዝነው የአብሮነት ሳምንት “ብዝሀነትን መኖር” በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ሲሆን ብልፅግና ፓርቲም የበአሉ አላማ ግቡን ይመታ ዘንድ የበኩሉን አስተዋፆ በማበርከት ላይ ይገኛል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤቱ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በአሉን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማክበር ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ስለ አብሮነት ፋይዳ ግንዛቤ ለመፍጠር በማለም ተናግረዋል።

እንደ ሀገር አብሮነትን በዘላቂነት ለመገንባት አስተሳሳሪ ትርክቶችን መገንባት ጠቃሚ መሆኑንና የተናጥልነት ክፍተትን ለመሙላት እጅግ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

ድህነት፣ ኋላ ቀርነት፣ጦርነት ከአብሮነት መላላት ጋር የሚመጡ ችግሮች መሆናቸውን ያነሱት አቶ ኢሳቅ በዘላቂነት ለእነዚህ ጉዳዮች እልባት መስጠት እንዲቻል የአብሮነትን ባህል መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *