የወሳኝ ኩነት ምዝገባ በአዋጅ ቁጥር 84/2008ዓ/ም ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ልደት፣ሞት፣ጋብቻ፣ፍቺ፣ጉድፈቻ ኩነቶችን በመመዝገብ እያደራጀ የሚገኝ እና ይህ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለማህበራዊ፣ለፖሊትካዊ፣ለኤኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ከሁሉም ተቋማት በቅንጅት ስራ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ የኤጀንሲው ቦርድ ስራ አመራር ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሀሚድ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ የሆነት አቶ ሽመልስ ለገሰ ስለወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅንስሃ ሳብና ጠቀሜታ እንዲሁም አስፈለጊት ዙርያ ለመድረኩ ተሳታፊ ሰነዱን አቅርቧል።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ ቅንጅታዊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ የኤጀንሲው ቦርዱአባላት ፣ቋሚ ኮሚቴ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከለሎች ክልል የራሳቸውን የክብር መመዝገብ ሹም የቀጠሮ በማሰራት ጥሩ አፈፃፀም ያለቸው መሆንገልፆ ለቀጣይ የኩነት ምዝገባ ወደ ዲጅታላይዜሽን ምዝገባ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ሃሳብ ተነስቷል ።
በቀጣይ በግንዛቤ ፈጠራ ላይ ትኩረት መስራት እና የኩነቶች ምዝገባ ስራዎች አሰገዳጅ መሆን እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
