ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ጉባኤው የክልሉን ምክር ቤት ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በመገምገም አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ጉባኤው የክልሉን ምክር ቤት ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በመገምገም አጽድቋል።

(የካቲት 12/2016 ዓ.ም) ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ጉባኤው የክልሉን ምክር ቤት ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በመገምገም አጽድቋል።

ትናንት የተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 9ኛ የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ የክልሉን ምክር ቤት ጽ/ቤት የበጀት ዓመቱን የ6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ገምግሞ አጽድቋል።

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ፣ ምክር ቤት የተጣለበትን የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሕጎችን የመደንገግ፣ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ አካላት የመከታተል፣ የመቆጣጠር የመደገፍ ኃላፊነት ለመወጣት አየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት 6 ወራት የምክር ቤቱ ቋሚ ቆሚቴዎች በአሶሳና መተከል ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎች በመገኘት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በሠላምና ልማት ያተኮረ የመስክ ምልከታ፣ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

የክልል ሴክተር መ/ቤት የአፈጻጸም ሪፖርት በቋሚ ኮሚቴዎች መገምገሙንም ዶ/ር ተመስገን ጨምረው ጠቅሰዋል።

የፍትህ ሥርዓቱን ለማሻሻል በክልሉ ምክር ቤት አስተባባሪነት የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የትራንስፎርሜሽን እና የፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደሥራ ተገብቷል ብለዋል።

ወደ ሥራ የተገባው የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የትራንስፎርሜሽን እና የፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ትግበራና ውጤታማነት የምክር ቤት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *