ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በ ኡንድሉ ወረዳ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች ለተወጣጡ አመራሮች ሲሆን የተሰጠውም ህዳር 17/2016ዓ.ም ነው፡፡
የወሳኝ ኩነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የመልካም አስተዳደር ፤ ሠላምና ዲሞክራሲ ለማስፈን አስፈላጊነቱ እጅግ ላቅ ያለ በመሆኑ የአመራሩን ግንዛቤ በማስፋት ወደ ወሳኝ ኩነት መረጃ አያያዝ መግባት አስፈላጊ መሆኑ በስልጠናው ላይ ተገልጸዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የቤ.ጉ.ክ.መ ወሳኝ ኩነት የትም/እና ስልጠና አሰልጣኝ አቶ ሽመልስ ለገሠ በስልጠናው ላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለጤና ፤ ለትምህርት ፤ለልማት ለህግና አስተዳደራዊ ሥራዎች መሠረት በመሆኑ አመራሩ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ሥልጠናውን መሥጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኞቹም የወሳኝ ኩነት ጥቅምን በመረዳት ለተግባራዊነቱና ለአፈጻጸሙ የበኩላቸውን ሚና በመወጣት እንደሚሰሩ ተስማምተዋል፡፡
