የቤኒሸጉል ጉሙዝ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በባምባሲ ከተማ በመገኘት ስልጠና ተሰጠ!

የቤኒሸጉል ጉሙዝ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በባምባሲ ከተማ በመገኘት ስልጠና ተሰጠ
በስልጠናው ላይ የተሳተፉት በወረዳው ላይ ለሚገኙ ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ላሉ አመራሮች ነው፡፡
ስልጠናውን የሰጡትም የቤኒሸጉል ጉሙዝ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አሰልጣኝ አቶ ሽመልስ ለገሰ ናቸው።
የስልጠናው ዋና አላማ በሀገሪቱ አጋጥሞ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክኒያ ተቋርጦ የነበረው የኩነቶች ምዝገባ ለማነቃቃት እና ወደ ነበረበት ደረጃ ለመመለስ መሆኑን በስልጠናው ላይ ተነስተዋል፡፡
አመራሩም የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በስልጠናው ላይ ተገልጿል ፡፡
የወረዳው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤገንሲ ባለሙያዎች ሚናስ በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ሀሳቦች እየተነሱ ተግዳሮቶች የሚልዋቸውን እንደ ተሽከሪካሪ፤ የበጀት ማነስ በማንሳት ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎችን በመስጠት ተወያይተውበታል፡፡
በመጨረሻም የተለያዩ አመራሮች እንደተናገሩት ከስልጠናው እጅግ በርካታ ጥቅሞች እንዳገኙና ከዚህ በፊት የነበሩባቸውን ብዥታዎች እንደጠራላቸው ተናግረዋል፡፡ከዚህ በኃላም ሁሉም ባለድርሻ አካላትቶች ድርሻቸውን በመወጣት ከባለሙያዎች ጎን በመሰለፍ አመራራዊ ድጋፍ እንዲደርጉ እና የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የቤኒሸጉል ጉሙዝ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የመረጃ ቅበላ እናጥንቅር ዳ/ሬት አቶ አለሚን ሱሌማን ተናግረዋል፡፡
ኤጄንሲውም ይህን መሰል ስልጠና የመጀመሪያው ባይሆንም የግንዛቤ ፈጠራው ይቀጥላል ብለዋል፡፡