በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአማራ ክልልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በተገኙበት ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
ህዝባዊ ውይይቱ “ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ነው በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው፡፡
በውይይቱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል ፡፡
ህዝባዊ ውይይቱ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች የሚነሱበትና ሰላም ፍቅርና አንድነትን የሚያጎለብቱ ሀሳቦች የሚነሱበት ነው፡፡
በውይይቱ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ህዝባዊ ውይይቱን እየመሩ ነው፡፡
EBC ዘግቦታል
በጀማል አህመድ